አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ያስተማራቸውን የዲግሪና የዲፕሎማ መርሃ ግብር ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ!

👉 ​አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ያስተማራቸውን የዲግሪና የዲፕሎማ መርሃ ግብር ተማሪዎች በአወሊያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

👉​ ኮሌጁ በዲፕሎማ መርሃ ግብር ለ11ኛ ዙር እንዲሁም በዲግሪ መርሃ ግብር ለ3ኛ ዙር በአጠቃላይ 68 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሀጂ ጀማል ፈንታው የኮሌጁን አፈጻጸምና የሥራ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤ ኮሌጁ ከ20 ዓመታት በላይ በትምህርት ዘርፍ በማገልገል ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ምሩቃንን ማፍራቱን ገልጸዋል።

አክለውም ኮሌጁ በቅርብ ዓመታት የሙያ ብቃት ምዘና (COC) እና የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ፈተናን መቶ በመቶ በማሳለፍ የተመራጭነት ደረጃውን እያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል።

👉​ የኮሌጁ ምክትል ዲን ኡስታዝ ናስር ዩሱፍ በበኩላቸው፤ በ2018 ዓ.ል የመምህራን ማሰልጠኛ መርሃ ግብር መጀመሩን አስታውሰው ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

👉 ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባም በቅርቡ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።

የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀማል መሐመድም ኮሌጁን ይበልጥ ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በመድረኩ ላይ ገልፀዋል።

👉​ በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታላላቅ ዑለማዎች፣ የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የኮሌጁ ኃላፊዎች እና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

​አወሊያ ቴሌግራም

👉t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *