Sheh Abdurehman Bin Mubarek (Abudujen) Visit Awolia!

ሼህ አብዱረህማን ቢን ሙባረክ (አቡዱጄይን) በአወሊያ የምስጋና ምሳ ግብዣ እና የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው!

ቀን ሐሙስ መስከረም 14/2019

👉 አለም አቀፍ እስላማዊ ዕርዳታ ድርጅት (IIRO) አወሊያን በሚያስተዳድርበት ዘመን የአወሊያ አስተዳደር የነበሩት ሼህ አብዱረህማ ቢን ሙባረክ (አቡዱጄይን) አወሊያ በመገኘት የቀድሞ ቤታቸው ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

👉 ሸህ አብዱረህማን አወሊያን በሚያስተዳድሩበት ግዜ ትልልቅ ስራዎች መስራት የቻሉ ታለቅ መሪ ነበሩ!

👉 በአወሊያ ውስጥ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራትም ትልቅ አስተዋፅኦ የነበራቸው ሲሆን ለአወሊያ ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

👉 ከተለያዩ ክፍለ ሀገር አይታሞችን በመሰብሰብ ያለ ምንም ሀሳብ ዲን እና አለማዊ ትምህርት ያለ ሀሳብ እንዲማሩ በማድረግ

👉 የቁርዓን ሃፊዞችን በማፍራት

👉 የተለያዩ ክፍለ ሀገር በመሄድ አቅመ ደካማዎች እንዲረዱ አድርገዋል።

👉 የአወሊያ መስጂድን ያስገነቡ

👉 በአወሊያ የጀናዛ ዕጥበት እንዲጀመር ያስደረጉ

👉 የአወሊያ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለአወሊያ እና ለአከባቢው ማህበረሰብ እስከ ዛሬ የምንጠጣውን እና የምንጠቀመውን ያበረከቱልን

👉 አወሊያ ኮሌጅ የከፈቱ

👉 አወሊያ ሆስፒታል ያስገነቡ

👉 የአወሊያ ትምህርት ቤቶችን እንዲስፋፋ እና ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ ያስደረጉ

👉 እንዲሁም አዚ ላይ ተጠቅሰው የማያልቁ የተለያዩ የዕርዳታ እና የልማት ስራዎችን በመስራት ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለቤታችን አወሊያ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

👉 ይሄንንም በማስመልከት ከ19 አመታት ብኋላ ወደ ቤታቸው አወሊያ በመመለሳቸው በማስመልከት በዛሬው እለት የምሳ ግብዣ እና የእውቅና ሽልማት በአወሊያ ተደርጎላቸዋል።

👉 ዛሬ በነበረው የምስጋና ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት ሸህ አብዱረህማን ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በመቀጠልም ከዚህ በፊት በአወሊያ እንደሰራነው ሁሉ ከአላህ ተውፊቅ ጋር አቅማቸው የሚችለውን በማድረግ አወሊያ እና ኢትዮጵያን ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

👉 በመጨረሻም የኢትዮጵያዊነት ባህላችን መገለጫ የሆነውን የጋቢ ስጦታ ከአወሊያ ተበርክቶላቸዋል።

ሁላችንም ለአወሊያ አባት ለሆኑት ለሼህ አብዱረህማን ቢን ሙባረክ በያለንበት ዱዓ እንድናደርግላቸው።

አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስላቸው።

አላህ ዲን የሚካድሙበት ረጅም እድሜ ከኢማን አፊያ ጋር ይስጣቸው።

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *