በሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑክ በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የሥራ ጉብኝት አደረገ።

👉 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማትና ማሕበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝደንት በሸይኽ ሐሚድ ሙሳ የተመራ ልዑክ አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ላይ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎችን ጎብኝቷል።

ግንቦት 11 / 2018 ዓ.ል
ዙል-ሂጃዕ 2/1447 ዓ.ሂ

👉 ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ የመሩት ልዑኩ ፒያሳ የሚገኘውን አወሊያ ቁ.1 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመጎብኘት የጀመሩ ሲሆን ልዑኩ ትምህርት ቤቱ በቅርቡ በምትክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቀበለውን ተለዋጭ ቦታም በተመሳሳይ ጉብኝት ማድረግ ችሏል።

👉 የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ ልዑክ በአንድ ግቢ በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘውን እና ዊንጌት አካባቢ በሚገኘው አወሊያ ዋና ግቢ በመገኘት እየተሰጡ ያሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን እና የስራ እንቅስቃሴዎችን መጎብኘት ችሏል።

👉 የአወሊያ ጤና ጣቢያ፣ የአረብኛ ቋንቋ ኮሌጅ እና የተማሪዎች ማደሪያ፣ ከቅድመ አንደኛ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የጀናዛ እጥበት አገልግሎት፣ የእንጨትና የብረታ ብረት ወርክሾፕ፣ የአስተዳደር ቢሮዎችና ሌሎች ማዕከላት በልዑኩ ተጎብኝተዋል።

👉 በተጨማሪም የዐብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም የቁርአን ማህበር አይነስውራን ተማሪዎች ማደሪያ ተጎብኝቷል።

👉 በጉብኝቱ ወቅት የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ አሁን ያለበት ደረጃ መድረስ እንደቻለ የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጂ ሰዒድ አስማረ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑክ አብራርተዋል።

👉 ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች በጽናት ተቋቁሞ ዛሬም የተለያዩ ማኅበራዊና መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ለማኅበረሰቡ እየሰጠ ይገኛልም ሲሉ ሀጅ ሰኢድ አስማረ አክለዋል።

👉 ድርጅቱ የጀናዛ እጥበትና የቀብር ማስፈፀም አገልግሎት፣ የንፁህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ለአከባቢው ማህበረሰብ፣ ክፍያ ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች  እና ለ20 አይነ ስውራን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እየሰጠ እንደገሚኝም ተገልጿል።

👉 በጉብኝቱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚዎችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የአወሊያ ማኔጅመንት አባላት፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምሕራንና ተማሪዎች ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።

👉 በመጨረሻም በቅርቡ እድሳቱ አልቆ የተለያዩ ዘመናዊ የጥርስ ማሽኖችን በማማላት ለአገልግሎት ክፍት የሆነውን የአወሊያ ጤና ጣቢያ “ጥርስ ክፍል” መርቀው ከፍተዋል።

አወሊያ ቴሌግራም
👉 https://t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *