ህብረት ባንክ ከወለድ ነጻ አግልግሎት ለአንጋፋው አወሊያ 3 ሚሊዪን ብር  ለግሷል

ህብረት ባንክ ከወለድ ነጻ አግልግሎት ለአንጋፋው አወሊያ 3 ሚሊዮን ብር ለግሷል

—————//—————————

👉 በበጎ አድራጎት አገልግሎት ለረዥም አመታት በጽናት ህዝብን እያገለገሉ ከሚገኙ ተቋማት በቀዳሚነት የሚገኘው አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የውድድሩን መስፈርት በከፍተኛ ሁኔታ በማሟላት ጥቅምት 13/2018 ዓ.ል በሸራተን አዲስ በተካሄደው ልዩ የድጋፍ መርሃ ግብር ከህብረት ባንክ  ከወለድ ነጻ አገልግሎት የ3 ሚሊዮን ብር ተሻላሚ ሆኗል።

👉 በሀገራችን ከ4 ሺህ በላይ አለማቀፍና ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚገኙ ቢሆንም በአላማቸው ጸንተው፣ በርካታ ተግዳሮቶችን ተቋቁመው የሚዘልቁት ግን ውስኖች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የባንኩን መመዘኛ ካለፉት 10 የበጎ አድራጎት ተቋማት መካከል አንጋፋው አወሊያ አንደኛው መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

👉 በሸራተን አዲስ በክብር እንግድነት ተጋብዘው በመገኘት ሽልማቱን የተቀበሉት  የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ሰይድ አስማረ  ባደረጉት ንግግር ወደ አዲስ ምዕራፍ በመሸጋገር ላይ የሚገኘው አወሊያ ላለፉት 72 አመታት በትምህርት፣ በጤናና በበጎ አድራጉት ስራዎች በመሰማራት  ማህበራዊ ሃላፊነቱን በሚገባ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ በዘንድሮ አመት

👉 በሁሉም ካምፓሶች ከ5250 በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በዝቅተኛ ክፍያ  በማስተማር በመልካም ስነ ምግባር የታነጹ ዜጋ በማፍራት ላይ  ተግተው እንደሚሰሩ ከነዚህ መካከል 800 አቅመ ደካማና ወላጅ አልባ ተማሪዎችን በነፃ (ያለክፍያ) እንደሚያስተምር

👉 በሁሉም ጤና ጣቢያዎቻቸው በተመጣጣኝ ክፍያ የጤና አግልግሎት እንደሚሰጥ

👉 ከ320 በላይ ለሚሆኑ ለአካባቢው  ማህበረሰብ በየቀኑ ነፃ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት እንደሚሰጥ

👉 በየቀኑ ነፃ የአስከሬን(ጀናዛ) እጥበትና የቀብር አገልግሎት እንደሚሰጥ

👉 ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካሞች የምግብ ማጋራት ስራዎች  ሳይቋረጡ ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸው

👉 ተቋሙ 512  ቋሚና ኮንትራት ሰራተኞች ያሉት ሲሆን
እንደዚህ አይነት ድጋፎችና እውቅና የበለጠ ህዝባችንን እንድናገለግል ሞራልና አቅም ስለሚሆኑን ሌሎች ባንኮች የህበረት ባንክን አርአያ መከተል እንዳለባቸው በመጠቆም ለህብረት ባንክ አመራሮች በድርጅታቸው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

👉 ሀጅ ሰይድ  አያይዘውም  “ ከአወሊያ ጋር መስራት ከመላው  ኢትዩዽያን ሙስሊሞች ጋር መስራት “ መሆኑን እንዲሁም  “አወሊያን መደገፍ ሀገርን መደገፍ “ መሆኑን ሁሉም የባለድርሻ አካላት እንዲገነዘቡት እወዳለሁ ብለዋል።

👉 በመርሃ ግብሩም ከቀረቡት ዶክመንታሪ ፊልሞች በአወሊያ ነሽዳ  ታጅቦ ለ10 ደቂቃ የቀረበው አወሊያ በተግባር የሰራቸውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዶክመንታሪ በሽራተን  ላሊበላ አዳራሽ የተገኘውን ታዳሚ በማስደሰቱ በከፍተኛ ጭብጨባ ምስጋና ቀርቦለታል ።

አወሊያ ቴሌግራም
👉 https://t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *