አዋሽ ባንክ ባዘጋጀው የረመዳን ኢፍጣር መርሀ-ግብር ላይ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች(አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ጨምሮ) ለተለያዩ ተቋማት ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

ቀን መጋቢት 6፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 16፣ 1446 ዓ.ሒ

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዋሽ ባንክ ባዘጋጀው የረመዳን ኢፍጣር መርሀ-ግብር ላይ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች(አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ጨምሮ) ለተለያዩ ተቋማት ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

አዋሽ ባንክ በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀውና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ለተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶችና ተቋማት የ23.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ባንኩ

  1. ለአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት የፕሮጀክት ማጠናከሪያ አምሰት ሚሊዬን ብር፣
  2. ለታላቁ አንዋር መስጅድ የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሰባት ሚሊዬን ብር፣
  3. ለኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የኩላሊት ህክምና ታካሚዎች የአንድ አመት ክፍያ 6.9 ሚሊዬን ብር እንዲሁም
  4. ለአሚን ሆስፒታል 12 የኩላሊት ህመም ታካሚዎች የአንድ አመት ክፍያ 4.6 ሚሊዬን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የገንዘብ ድጋፉ በተቋማት በኩል ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል በማሰብ የተደረገ የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባር ሲሆን ባንኩ ድጋፉን ያደረገው በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በኩል ነው።

ቴሌግራም t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *