የኢትዬጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የአወሊያ ወሊሶ ሕፃናት መንደር ጉብኝት
የካቲት 20፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 28 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ልዑክ የአወሊያ ወሊሶን የሕፃናት መንደር የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ልዑክ የአወሊያ ዕዳታና ልማት ድርጅት ስር የሚተዳደረውን የወሊሶ የሕፃናት መንደር ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።
ልዑኩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማት ክንፍ አንዱ በሆነው የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የወሊሶ ቅርንጫፍ የህፃናት መንደርን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ይገኛል።
በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ጋሊ ሙኽታር እና የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ አባላትና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።
