• አወልያን በአጭር sms code እንዴት መርዳት ይቻላል?
    ወደ 7500 ይላኩ!
  • አወልያ የጤና ማዕከል በፊት ከሚሰጣቸው አገልግሎት ቢገለፅ?
    እስከ 2002 ድረስ በአማካኝ 414 እናቶች የቅድመ ወሊድ ተጠቃሚ፤107 እናቶችና ህጻናት የክትባት አገልግሎት፤ 20 እናቶች የወሊድ አገልግሎት፤ 23 ታካሚዎች የሳምባነቀርሳ ክትትል አገልግሎት፤ 23 ግለሰቦች የኤች.አይ.ቪ ምርመራና የምክር አገልግሎት፤180የጥርስ ታካሚዎችን፤ 1033 ላቭራቶሪ ተጠቃሚዎችን፤ 1000 የሚሆኑትን የመድሃኒት አገልግሎት፤ 900 ታካሚዎች በተመላላሽነት አገልግሎት ሰጥቷል።
  • አወልያ ህፅናት ማሳደግያ አገልግሎቱን መቼ ጀመረ?
    የአወሊያ ህጻናት ማሳደጊያ በአለም አቀፉ ኢስላማዊ እርዳታ ድርጀት ከቀድሞው ሠራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር ስር በነበረው የህጻናትና ወጣቶች ኮሚሽን ጋር በተደረገ የፕሮጀክት ስምምነት ታህሳስ 1984 ስራውን ጀመረ።