የሙስሊም ዲያስፖራ ልዑካን በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!
የሙስሊም ዲያስፖራ ልዑካን በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!
ቀን ጁምዓ ነሐሴ 8/2018
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ የሙስሊም ዲያስፖራ ተወካዮች፤ በአወሊያ ዕርዳታና ልማትና ድርጅት እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት፣ የትምህርትና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።
አወሊያ ከሰው ልጅ ውልደት ጀምሮ እስከ ሞት ድረስ ያለውን የሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ የተለያዩ የሰው ልጅ ፍላጎቶችን በአንድ ማዕከል አጠቃሎ አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛ ኢስላማዊ ተቋም መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተብራርቷል።
የዲያስፖራ ተወካዮቹ በድርጅታችን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ያደነቁ ሲሆን፤ “ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስንጎበኝ የተሰማንን ደስታ፣ በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ሥራዎች ላይ በድጋሚ አረጋግጠናል” በማለት የተቋማችንን ዳግም ማንሰራራት አድንቀዋል።
አክለውም አወሊያ ዕድሜ ጠገብ ተቋም እንደመሆኑ፣ ታሪኩን የሚመጥን ሥራ ለማከናወን በአመራሩ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚደግፉና ከድርጅቱ ጎን እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉት የዲያስፖራ ተወካዮች መካከል፦
ኡስታዝ ሙክታር ጀማል (በእንግሊዝ የነጃሺ መስጂድ ኢማም)
ማህሙድ ሳዲቅ (በካናዳ ቶሮንቶ የኖርዝ ኢስላሚክ ሴንተር ሊቀመንበር)
አሳድ ሙሐመድ (በስዊድን የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወካይ)
ሙሐመድ ደጉ (የፈርስት ሂጅራ መስጂድ ኢማም)
ነዋዊ ሙሳ (የደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ማህበር ሊቀመንበርና ተወካይ)
አብዱራዛቅ ሙሐመድ (የኦሮሞ ማህበር ሊቀመንበር) እና
ኢንጅነር አሊ ላሳን (በስዊድን የአፋር ማህበር ተወካይ) ይገኙበታል።
አወሊያ ቴሌግራም
