ዜና አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች
📚 ዜና አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች
👉 ለ2 ቀናት ጥር 10 እና 11 /2017 (ቅዳሜ እና አሁድ) በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ መሰረት ያደረገው ግምገማ፣ ወይይት አለት ሆኖ አልፏል።
👉 ከጋላክሲ ትምህርት ስልጠናና ማማከር አገልግሎት ጋር የሚዘጋጀው እስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ግምገማው የአወሊያ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገበት ሲሆን
👉 አጠቃላይ የእቅድ ዝግጁቱ የደረሰበት ደረጃ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።
👉 ዶ/ር ጀማል መሀመድ የአ.ዕ.ል.ድ የቦርድ ሰብሳቢ በሁለቱ ቀናት የነበረው ቆይታ ለትምህርት ቤቱ እየተሰራ ያለው ስትራቴጂክ እቅድ ትልቅ ጥቅም እና ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን
👉 የአ.ዕ.ል.ድ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ሰኢድ አስማረ በበኩላቸው የሁለቱ ቀን ቆይታ የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ ግለሰቦች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ስልጠና ለሰጡት ለዶ/ር ጀማል እና ለአቶ አብዱልኳሊቅ ምስጋና አቅርበዋል።
እቅዱን በዋናነት ለሚያዘጋጁት ጋላክሲ ትምህርት ስልጠናና ማማከር አገልግሎት ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለአወሊያ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር (አልሙኒ) የእቅድ ስራው እንዲሳካ ለሚያደርጉት ጥረት በማመስገን ውይይቱ በዛሬ እለት ተጠናቋል።
👉 አወሊያ ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5
አወሊያ ት/ት ቤት Facebook👇👇👇
👉https://www.facebook.com/Awoliaschool5
