ማሻአላህ!

ቀን 24/03/2016 E.C

👉 የአወሊያ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር(አልሙኒ) በ2015 ዓ/ል 12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ እንዲሁም በቀጥታ ወደ መረጡት የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ አመት ተማሪ ሆነው የተመደቡ 7 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት 30,000 ብር በአልሙኒ ሰብሳቢ በወንድም መሀመድ በድሩ አማካኝነት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህም መሰረት

1 ሂክማ ያሲን = 6000 ብር

2 ሃፍሷ አብዱልጀሊል = 5000 ብር

3 መሀመድሰኢድ ሙስጠፋ =4000 ብር

4 ዑመር አሰን = 3000 ብር

5 ረዋን አወል = 3000 ብር

6 ሃውለት እድሪስ = 3000 ብር

7 ሚና ቡሴር = 3000 ብር

👉 በተጨማሪም የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጂ ሰኢድ አስማረ በድርጅቱ ስም 1ኛ ለወጣች ተማሪ ሂክማ ያሲን የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም ለሁሉም ተማሪዎች የሚከፋፈል 19,000 ብር እንደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ርቀት በመመልክት የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል።

በዚህም መሰረት

1 ሂክማ ያሲን = 5000 ብር

2 ሃፍሷ አብዱልጀሊል = 2000 ብር

3 መሀመድሰኢድ ሙስጠፋ =2000 ብር

4 ዑመር አሰን = 3000 ብር

5 ረዋን አወል = 2000 ብር

6 ሃውለት እድሪስ = 3000 ብር

7 ሚና ቡሴር = 2000 ብር

👉 ተማሪዎቹም ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ሽልማታቸውን በዛሬው እለት ተቀብለዋል።

👉 የአወሊያ ሁ/ደ/ት/ቤትም ለሁሉም ተማሪዎች የዕውቅና እና የምስጋና ሰርተፊኬት አበርክቶላቸዋል።

ልዩ ተሸላሚ

👉 መምህርት በድሪያ አብዱረዛቅ ተማሪዎችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ተማሪዎቹ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ በማስቻሏ በአልሙኒ በኩል 3000 ብር እና በአ/ዕ/ል/ድ በኩል 5000 ብር ሽልማት ተበርክቶላታል።

አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት!

አወሊያ ቴሌግራም

👉t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *