በአሜሪካን ሃገር የሚገኘው ሙስሊም ኤድ ለአወልያ ሆስፒታል ከ2.7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!

ጥቅምት 06/2016 Or October 17/2023

አወልያ ልማትና እርዳታ ድርጅት ለረጅም አመታት በትምህርት ፣በጤናና እርዳታ ሥራዎች ተሰማርቶ ለበርካታ አመታት ማህበረሰቡን በማገልገል የሚገኝ ሲሆን በጤናው ዘርፍም አወልያ ጤና ጣቢያ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ለሆስፒታሉ የሚያስፈልጉ

መሳሪያዎች መካከል ደረጃውን የጠበቀ አልጋ አንዱ በመሆኑ በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው

ሙስሊም ኤድ ግምታቸው ከ2.7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡትን 90 አልጋዎችን ፣20Iv ፖል, 25ኦቨር ፖል በዕርዳታ መልክ አበርክቷል።

በዚህ የርክክብ መርሐግብር ላይ ኢንጂነር አንዋር ሙስጠፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ትምህርትና ልማት ኃላፊ፣ ጀማል መሃመድ መሀመድ የአወልያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ሥራ አመራርና የቦርድ ሰብሳቢ፣ ዶክተር አንዋር ሙስጠፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባል፣ የአዋሽ ባንክ አወልያ ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ ኸድር እና የድርጅቱ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተያያዥነት አዋሽ ባንክ ኢክላስ የወለድ አልባ ባንክ አገልግሎት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአወልያ የልማት ድርጅት ለ321 ተማሪዎች የዩኒፎርም፣ ደብተር፣ የትምህርት ቤት ክፍያን ጨምሮ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

በዚህ የርክክብ መርሐግብር ላይ አወልያን እየደገፉ ላሉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ።

አወልያ የእርዳታና ልማት ድርጅት በአሁኑ ወቅት በ4ቱ ካምፓሶች 4200 ተማሪዎችን እና 450 ወላጅ ያጡ ተማሪዎችን በነፃ እያስተማረ ይገኛል።

ድርጅቱ 11 የቦርድ አባላት፣ ከ400 በላይ መምህራን ሕክምናና ድጋፍ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን በመርሐግብሩ ተገልጿል።

አወሊየ ቴሌግራም👇👇👇

👉t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *