Muslim World League President Visit Awolia!

ክቡር ዶክተር ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ  ከመጅሊሳቸው ጋር በጋራ በመሆን አወሊያን ተረክበው እንዲያስተዳድሩት ለዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አል ዒሳ ጥሪ አቀረቡ።

የዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ሊግ ዋና ፀሐፊ  ዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አል ዒሳ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች እና የአዲስ አበባ ከተማ መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዱዓቶች፣ ኢማሞች፣ ዑስታዞችና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በተገኙበት በአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ታላቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ክቡር ዶክተር ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ሊግ ዋና ፀሐፊ  ዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አል ዒሳ አወሊያን ተረክበው ከመጅሊሳቸው  በጋራ በመሆን እንደቀድሞው እንዲያስተዳድሩት ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

ዶክተር ሙሐመድ ቢን አብዱልከሪም አል ዒሳ በበኩላቸው በአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፒያሳ በሚገኘው የአወሊያ ቅጥር ግቢ ባለ 19 ፎቅ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኘችበት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

Awolia Telegram 👇👇👇
👉 t.me/awoliaschool5

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *