ድርጅታችን አወሊያ በትምህርት በጤናና እርዳታ ስራዎች ተሰማርቶ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሰኔ 2003 ጀምሮ

ድርጅታችን አወሊያ በትምህርት በጤናና እርዳታ ስራዎች ተሰማርቶ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሰኔ 2003 ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ም/ቤት እንዲያስተዳድረው ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ በአገልግሎቱም ሆነ በገቢው እየተዳከመ በመምጣቱ ደመወዝ መክፈል እንኳን እስኪያቅተው ደርሷል፡፡በዚሁ ምክንያት የስራ አመራር ቦርዱ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እቅድ በማዘጋጀት ወደ ህዝባችን ለመግባት ወስነ፡፡ከጥቅምት 2013 ጀምሮ አወሊያን በማዳን ጥሪ ሀገር አቀፍና አለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ማካሄዳችን ይታወቃል፡፡በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶችን በማስተባብር ባገኘነው ገንዘብ የተለያዩ ስራዎችን አከናውነናል፡፡ 👉 በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ምን ተገኘ፤ በተገኘው ገንዘብስ ምን ምን ስራዎች ተሰሩ የሚል አጠቃላይ ሪፖርት ይቀርባል፡፡ 👉 በተገኘው ገንዘብ ተሰርተው የተጠናቀቁ ህንጻዎችን ማስመረቅ እንዲሁም ቀሪ ስራዎቻችን የደረሱበትን በማስጎብኘት በፍጥነት የሚያልቁበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡ 👉 በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በገንዘባቸው፤ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው ለተሳተፉ በውጪ ሀገርም ሆነ ሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች የምስጋና መርሃግብር ተካቷዋል፡፡ 👉 በመጨረሻም አወሊያ ራሱን ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ሁሉ ከአሁኑ በበለጠ መላው ሙስሊም ማህበረሰብ በባለቤትነት ስሜት ትብብርና ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት የሚተላለፍበት ይሆናል፡፡ በመሆኑም ሚያዚያ 9/2014 ከጧቱ 3፡00 ሰአት ጀምሮ በሚካሄደው የህንጻ ምርቃትና፣ የቀሪ ስራዎች ጉብኝትና ምስጋና ፕሮግራም ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ ተጋብዟል፡፡አወሊያን ከማዳን ጥሪ አወሊያን ወደ ማሻገር የሄድን ስለሆን የሁላችንም ለሆነችው አወሊያ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከጎኗ መቆም የሁሉም ኃላፊት መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ሚያዚያ 9/2014 እሁድ 3፡00 ሰአት ጀምሮ በአወሊያ ዋናው ግቢ እንገናኝ!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *