በትላንትናው ዕለት እሁድ ሚያዝያ 9/2014 ዓ/ል በአወሊያ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የምርቃት፣ የጉብኝት፣

👉 በዚህም ፕሮግራም ላይ በቀድሞ የአወሊያ ተማሪዎች ማህበር (አልሙኒ) አማካኝነት አንድ የቀድሞ የአወሊያ ተማሪ የአወሊያ ሆስፒታልን ዘመናዊ ደረጃውን የጠበቅ ሊፍት (አሳንሱር) ግማሽ ክፍያ ማለትም ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር (2,500.000 ብር) ከፍሎ ለመስራት ቃል የገባ ሲሆን፤👉 እንዲሁም አንዲት ስሟ እንዳይጠቀስ የፈለገች እህታችን አምስት መቶ ሺ ብር (500,000 ብር) ነይታለች፡፡👉 ሸህ ሱልጣን አማን (የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት) ሁለት መቶ ሺ ብር (200,000 ብር) ነይተዋል፤👉 ዑስታዝ አቡበከር አህመድ አንድ መቶ ሺ ብር (100,000 ብር) ነይተዋል👉 ዑስታዝ አህመዲን ጀበል አንድ መቶ ሺ ብር (100,000 ብር) ነይተዋል👉 ዶክተር ጀይላን ከድር (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት) ሃምሳ ሺ ብር (50,000 ብር) ነይተዋል👉 ሸህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ (የኦሮሚያ ክልል መጅሊስ ፕሮዝዳንት) ሃምሳ ሺ ብር (50,000 ብር) ነይተዋል👉 ሸህ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ አስር ሺ ብር (10,000 ብር) ነይተዋል👉 የታሪክ ተመራማሪው ኢብራሂም ሙሉሸዋ ሰላሳ ሺ ብር (30,000 ብር)👉 አንዲት እህታችንም የጣት ቀለበቷል ሰጥታለችእንዲሆም ሌሎች ወንድም እና እህቶች ከ100 ብር ጀምሮ በካሽ በመስጠት እና ኒያ በማድረግ ለአወሊያ ያላቸውን አለኝታነታቸውን አሳይተዋል፡፡ሌሎችም የተለያዩ ጅምር ላይ ያሉ የተለያዩ የሆስፒታል ያልተጠናቀቁ ስራዎች ወደ ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ብር ገደማ የሚገመቱ (33,000.000) ስላሉ ሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በገንዘቡ፣ በዕውቀቱ፣ በጉልበቱ እና በሌሎችም ነገራቶች በመሳተፍ ብቸኛው እና የመጀመሪያ የሆነችውን አወሊያችንን በማገዝ ቀድሞ ወደነበረችበት ከፍታ እንድንመልሳት ለማለት እንወዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *